እንኳን ወደ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የመስመር ላይ የተሳትፎ ማዕከል በደህና መጡ

የሲያትል የማመላለሻ ፕላን (STP) በሲያትል ውስጥ የወደፊት የማመላለሻ ራዕይ ነው።

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ሁሉም ሰው ቦታዎችን እና እድሎችን ለመድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና ተመጣጣኝ አማራጮችን የሚያቀርብ የማመላለሻ ስርዓት ለመገንባት ያለን ቁርጠኝነት ነው። STP ለቀጣዮቹ 20 ዓመታት የሀገር ውስጥ የማመላለሻ መዋዕለ ንዋዮችን ይመራል – ስለዚህ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን!

የኛ የማመላለሻ ስርዓታችን ከመንገዶች በላይ ነው። የእግረኛ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ደረጃዎችን፣ የሕዝብ ማመላለሻዎችን፣ ማለፊያዎችን እና መንገዶችን፣ የብስክሌት መስመሮችን፣ የእግረኛ ማቋረጫ መንገዶችን፣ እንደ የመንገድ ካፌዎች እና ወንበሮች ያሉ የህዝብ ቦታዎችን እና ሌሎችንም ያካትታል። የመጓጓዣ ስርዓቱ ከቦታዎች እና እድሎች ጋር እያገናኘ፣ ሁሉም ሰው በከተማው ውስጥ የሚዘዋወርበት ነው። ነገር ግን ኮቪድ-19፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ እና ፈጣን የህዝብ ቁጥር መጨመር ይህ ስርአት ያለችግር እንዲሄድ አስቸጋሪ ያደርጉታል። ለዚህም ነው አሁን እና ወደፊት የሚሰራ ዘላቂ ስርዓት መፍጠር የምንፈልገው።

እንደተገናኙ ይቆዩ

ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ:

እቅዱ ምን እንደሆነ የበለጠ ለማወቅ፣ የፕሮጀክት ግብዓቶችን እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ለማግኘት እና በእቅድ ሂደቱ ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የሲያትል የማመላለሻ ፕላን ድህረ ገጽን ይጎብኙ።

በሲያትል የወደፊት የመጓጓዣ እቅድ ማውጣት ውስጥ ይሳተፉ!

በመጀመርያው የተሳትፎ ምዕራፍ፣ ከፀደይ እስከ ክረምት 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ከእርስዎ ጋር አብሮ ይሰራል – ማህበረሰቡ – በሲያትል የወደፊት የመጓጓዣ ራዕይን በጋራ ለመመስረት፣ እርስዎ በከተማው ዙሪያ ሲንቀሳቀሱ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች፣ ተግዳሮቶች እና ፍላጎቶች ለመረዳት እርስዎን ማዳመጥ።

“በሲያትል ውስጥ ለወደፊቱ የመጓጓዣ የጋራ ራዕይ” ስንል ምን ማለታችን ነው? የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) ሁላችንም ወደፊት እንዴት በከተማ ዙሪያ መንቀሳቀስ እንደምንፈልግ ለመገመት ለኛ እድሉ ነው። የሁሉንም ሰው ፍላጎት የሚያሟላ የመንገድ እና የህዝብ ቦታዎች መረብን ለመገንባት ስለእርስዎ ሃሳቦች፣ ልምዶች፣ ተግዳሮቶች እና እድሎች ለመስማት ተስፋ እናደርጋለን።

ማወቅ እንፈልጋለን:

  • በሲያትል ስላለው የመጓጓዣ የወደፊት ሁኔታ ሲያስቡ፣ ምን ለማየት ተስፋ ያደርጋሉ? ለእርስዎ አስፈላጊ ምንድነው?
  • በሲያትል አካባቢ ሲዘዋወሩ፣ ምን ችግሮች ያጋጥሙዎታል? መዘዋወርን ቀላል የሚያደርገው ምንድን ነው?

ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡዎትን መልሶች የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ መሰረት ለመገንባት እንጠቀማለን። በየሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) አፈጣጠር ውስጥ በመሳተፍ ለሁሉም ሰው በተሻለ ሁኔታ የሚሰራ የመጓጓዣ ስርዓት እንድንገነባ ይረዱናል!

የአሁኑን የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ የዳሰሳ ጥናታችንን ይውሰዱ

የመጀመሪያውን የዳሰሳ ጥናት ለወሰዱት ሁሉ እናመሰግናለን! የማህበረሰቡን ተደራሽነት ለማቀድ የእርስዎ ግብአት STP ን እንድናዳብር እና ረድቶናል።

የአሁኑ የዳሰሳ ጥናታችን የሚያተኩረው በሲያትል ውስጥ የወደፊት የመጓጓዣ አገልግሎት የጋራ ራዕይን በማቋቋም ላይ ነው። ስራችንን ለመምራት ምላሾችዎን ከዚህ በታች ያጋሩ!

በበይነተገናኝ ካርታችን ላይ ተግዳሮቶችን እና እድሎችን የት እንደሚያዩ ይንገሩን

ይህን ካርታ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል:

  • የመረጡትን ቋንቋ ለመምረጥ ይህን የትርጉም መግብርን የሚወክል አዶ በካርታው ላይአዶ ይጠቀሙ።
  • የመርፌ ንቁጥ፣ መስመር ወይም የአከባቢ ምልክት ማድረጊያን ወደ ካርታው ጎትተው ይጣሉ ወይም “አሁን አስተያየት ስጡ!” የሚለውን ይጫኑ።
  • በካርታው ላይ ምልክት ማድረጊያ አንዴ ካስቀመጡ በኋላ ልምዶቻችሁን፣ ቅድሚያ የምትሰጧቸውን ነገሮች፣ ተግዳሮቶች እና እድሎች በአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ውስጥ አካፍሉ እና “ቀጣይ” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
  • አስተያየትዎን ካጋሩን በኋላ፣ አማራጭ የዳሰሳ ጥናት ይታያል። ይህ መረጃ ለሁሉም የማህበረሰብ አባላት ያለንን አገልግሎት ለማሻሻል ይረዳናል።

በሚመጣው ክስተት ላይ ይገኙ

መጪ ምናባዊ እና በአካል የተሳትፎ እድሎች

ባሉበት እርስዎን መገናኘት!

መጪ ክንውኖችን በታቀደላቸው መሰረት እዚህ የቀን መቁጠሪያ ላይ እንለጥፋለን። በሚመጡት እድሎች ላይ ለመሳተፍ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት ይከታተሉ።

ወደ አርስዎ እንመጣለን!

ወደ ክስተቶችዎ እና ስብሰባዎችዎ እኛን ለመጋበዝ ይህንን ቅጽ ይጠቀሙ።

Invite us

የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) እየተካሄደ ባለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተደራሽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የተሳትፎ እድሎችን ለማስተናገድ ቁርጠኛ ነው። በአካል ለሚከሰቱ ክስተቶች የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል መመሪያዎችን እየተከታተልን እና በተቻለ ጊዜ ሁሉ ለተሳትፎ እድሎች ምናባዊ አማራጮችን እናቀርባለን።

ኢሜይል ይላኩልን ወይም በድምጽ መልእክት መስመራችንን ይደውሉ

ስለ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ጥያቄዎች፣ ስጋቶች ወይም አስተያየቶች አሉዎት? ኢሜይል ይላኩልን ወይም በድምጽ መልእክት ይተው እና እንደገና መልሰን እናገኝዎታለን።

የብዝሀን-ቋንቋ የስልክ መስመራችን ይደውሉ እና አስተያየትዎን ለማጋራት ወይም ጥያቄ ለመጠየቅ መልእክት ይተው። በመረጡት ቋንቋ መልእክት ይተዉ እና የኛ የስምሪት ቡድን ወይም አንድ አስተርጓሚ መልሶ ደውሎ ለጥያቄዎችዎ መልስ ይሰጥዎታል።

ኢሜይል ይላኩልን: STP@Seattle.gov

የእኛን የድምጽ መልዕክት መስመር ይደውሉ : 206-257-2114

አጠቃላይ አስተያየት ይተዉ

በሲያትል የትራንስፖርት እቅድ ላይ አጠቃላይ አስተያየት መስጠት ከፈለጉ፣ እባክዎን ይህንን የአስተያየት ሳጥን ይጠቀሙ።

አስተያየቶች

አስተያየቶች

ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የአካባቢ የአየር ንብረት ግምገማ ሂደት ምንድ ነው?

ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የአካባቢ የአየር ንብረት ግምገማ ሂደት ምንድ ነው?

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) በግዛት የአካባቢ የአየር ንብረት የአቋም መመሪያ ሕግ (SEPA) ግምገማ ሂደት ውስጥ ያልፋል። SEPA ዕቅድ በማውጣት እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች የአካባቢ ንብረት እሴቶችን በሚገባ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ያረጋግጣል።

የ SEPA መቃኘት የ30-ቀን አስተያየት ጊዜ – ሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2022: መቃኘት (Scoping) ማህበረሰቡ በአካባቢ ተጽእኖ መግለጫ ውስጥ ስለሚካተተው ግብአት ከSDOT ጋር እንዲያካፍል እድል ይሰጣል።

የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ ረቂቅ (EIS) የሚለቀቅበት እና የ30-ቀን አስተያየት ጊዜ — በ2023 መጀመሪያ: ረቂቁ EIS ከተለቀቀ በኋላ ማህበረሰቡ አስተያየቶችን እንዲያካፍል ተጋብዟል። እነዚህ አስተያየቶች፣ ከምላሾች ጋር በመጨረሻው EIS ውስጥ ተካተዋል።

የመጨረሻ EIS ታትሟል – በ2023 አጋማሽ ላይ: የመጨረሻው EIS፣ በረቂቁ EIS ላይ የተጋሩ አስተያየቶች ምላሾችን ያካተተ፣ የውሳኔ አሰጣጡን ሂደት ለማሳወቅ ይጠቅማል

ወዴት እያመራን እንዳለን

የዕቅድ ሂደቱ በጥር 2022 ተጀምሯል፣ እና በ2023 ጸደይ የህዝብ ግምገማ እቅድ ይኖረናል ብለን እንጠብቃለን። በሂደቱ ውስጥ፣ ልምዶችዎን ለመካፈል እና እቅዱን ለመገምገም፣ አስተያየት ለመስጠት እና ለማገዝ እድሎች ይኖሩዎታል፣ ስለዚህ በሂደቱ ላይ መልሰው ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጋር ያረጋግጡ።

የጊዜ መስመር

ጸደይ —
ክረምት 2022

የህዝብ ተሳትፎ ደረጃ 1 (እኛ እዚህ ነን)

በዚህ ደረጃ ወቅት ከእርስዎ ጋር አብረን — ማህበረሰቡ — ለ STP የጋራ ራዕይ ለመመስረት እንሰራለን። በሲያትል አካባቢ ሲዘዋወሩ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች፣ ተግዳሮቶችዎን እና ፍላጎቶችዎን ለመረዳት ከእርስዎ ጋር እንሰራለን።

በልግ 2022 —
ጸደይ 2023

ደረጃ 2 የሕዝብ ተሳታፊነት

በዚህ ደረጃ ወቅት፣ በደረጃ 1 የሰማነውንና የተማርነውን እና የእርስዎ ግብአት እስከዛሬ እቅዳችንን እንዴት እንዳሳወቀ እናካፍላለን። የተዘጋጁት የእቅዱ ክፍሎች እየዳበሩ ሲሄዱ ከማህበረሰቡም ተጨማሪ ግብአት እንፈልጋለን።

ጸደይ 2023

ክፍል 3 የሕዝብ ተሳታፊነት

በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችንን ለማረጋገጥ የSTP ረቂቁን ለማህበረሰቡ እናካፍላለን እና የእርስዎን ግምገማ እና አስተያየት እንጠይቃለን።

ክረምት 2023

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ይጨርሱ!

በሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) ዝመናዎች እና መጪ ዕድሎች ለመሳተፍ፣ ለኢሜይል ዝመናዎች መመዝገብዎን ያረጋግጡ።

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ?

እቅዱ ምን እንደሆነ የበለጠ ለማወቅ፣ የፕሮጀክት ግብዓቶችን እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ለማግኘት እና በእቅድ ሂደቱ ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የሲያትል የማመላለሻ ፕላን ድህረ ገጽን ይጎብኙ።

የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ለማዘጋጀት ስለተሳተፉ እናመሰግናለን! የጋራ ፍላጎታችንን የሚያሟላ የመጓጓዣ ስርዓት ለመፍጠር ከእርስዎ እና ከጎረቤቶችዎ ጋር መስራታችንን ለመቀጠል እንጠባበቃለን።

እንደተገናኙ ይቆዩ

ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ:

ጥያቄዎች፣ ስጋቶች ወይም አስተያየቶች አሉዎት?

ኢሜይል ይላኩልን: STP@Seattle.gov

የእኛን የድምጽ መልዕክት መስመር ይደውሉ: 206-257-2114