እንኳን ደህና መጡ
እንኳን ለሲያትሉ የማመላለሻ እቅድ የኦንላይን ላይ የተሳትፎ ማዕከል በደህና መጡ
የሲያትል የማመላለሻ ዕቅድ (STP) በሲያትል ውስጥ የወደፊት የማመላለሻ አንድ ራዕይ ነው።
የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ቦታዎችን እና እድሎችን ለመድረስ ሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አማራጮችን የሚያቀርብ አንድ የማመላለሻ ስርዓት ለመገንባት ያለን ቁርጠኝነት ነው። STP ለቀጣዮቹ 20 ዓመታት የሀገር ውስጥ የአካባቢ የማመላለሻ መዋዕለ ንዋዮችን ይመራል – ስለዚህ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን!
የኛ የማመላለሻ ስርዓታችን ከመንገዶች ብቻ በላይ ነው። የእግረኛ መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ደረጃዎችን፣ የሕዝብ ማመላለሻዎችን፣ ማለፊያዎችን እና መንገዶችን፣ የብስክሌት መስመሮችን፣ የእግረኛ ማቋረጫ መንገዶችን፣ እንደ የመንገድ ካፌዎች እና ወንበሮች ያሉ የህዝብ ቦታዎችን እና ሌሎችንም ያካትታል። የመጓጓዣ ስርዓቱ ከቦታዎች እና እድሎች ጋር እያገናኘ፣ ሁሉም ሰው በከተማው ውስጥ የሚዘዋወርበት ነው። ነገር ግን ኮቪድ-19፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ እና ፈጣን የህዝብ ቁጥር መጨመር ይህ ስርአት ያለችግር እንዲሄድ አስቸጋሪ ያደርጉታል። ለዚህም ነው አሁን እና ወደፊት የሚሰራ ዘላቂ ስርዓት መፍጠር የምንፈልገው።
እንደተገናኙ ይቆዩ
ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ:
የሲያትል የማመላለሻ እቅድን እኛ እንዴት አብረን እየፈጠርን ነው?
ዙር 1
ግንቦት – ነሐሴ 2022
ዙር 2A
መስከረም 2022–የካቲት 2023
ዙር 2B
ታሕሳስ 2022–የካቲት 2023
ዙር 3
ሚያዝያ – ሰኔ 2023
እርስዎን እየጠየቅን ያለን…
የመጓጓዣ ተግዳሮቶችዎን ይንገሩን ራዕይን፣ ግቦችን፣ አላማዎችን፣ ይገምግሙ፤ የመጓጓዣ የወደፊት እጣ ፈንታዎች፤ የድርጊቶች ምናሌ የመጀመሪያ ረቂቅ የአውታረ መረብ ካርታዎችን ይገምግሙ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ረቂቅን ይገምግሙ የእርስዎን ግብአት ለ… እንጠቀማለን
ረቂቅ ራዕይን፣ ግቦችን እና አላማዎችን ለማሳወቅ ረቂቅ ፖሊሲዎችን ለማጥራት የመጀመሪያ ረቂቅ ካርታዎችን ለማጥራት የመጨረሻውን ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለማደራጀት
እርስዎን እየጠየቅን ያለን…
ዙር 1 ግንቦት–ነሐሴ 2022
የመጓጓዣ ተግዳሮቶችዎን ይንገሩን
ዙር 2A መስከረም 2022–የካቲት 2023
ራዕይን፣ ግቦችን፣ አላማዎችን፣ ይገምግሙ፤ የመጓጓዣ የወደፊት እጣ ፈንታዎች፤ የድርጊቶች ምናሌ
ዙር 2B ታሕሳስ 2022–የካቲት 2023
የመጀመሪያ ረቂቅ የአውታረ መረብ ካርታዎችን ይገምግሙ
ዙር 3 ሚያዝያ–ሰኔ 2023
የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ረቂቅን ይገምግሙ
የእርስዎን ግብአት ለ… እንጠቀማለን
ዙር 1
ግንቦት – ነሐሴ 2022
ረቂቅ ራዕይን፣ ግቦችን እና አላማዎችን ለማሳወቅ
ዙር 2A መስከረም 2022–የካቲት 2023
ረቂቅ ፖሊሲዎችን ለማጥራት
ዙር 2B ታሕሳስ 2022–የካቲት 2023
የመጀመሪያ ረቂቅ ካርታዎችን ለማጥራት
ዙር 3 ሚያዝያ–ሰኔ 2023
የመጨረሻውን ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለማደራጀት
በሲያትል የማመላለሻ እቅድ ውስጥ ያለው እኩልነት
ያለፉትን እና በአሁን ወቅት የውሳኔ አሰጣጥ አወቃቀሮች እና መዋዕለ ንዋዮች የታሰቡበትም ሆነ እና ያልተጠበቁ ውጤቶችን ጨምሮ ፍትሃዊ እኩልነት የሌላቸው ስርዓቶች ተፅእኖዎችን እንገነዘባለን። በሲያትል የማመላለሻ እቅድ በኩል፣ እኛ የምንፈልገው ምንም ተጨማሪ ጉዳት ላለማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ያለፉት ፖሊሲዎቻችን፣ አሰራሮቻችን እና ፕሮግራሞቻችን ያስከተሉትን ታሪካዊ ጉዳቶችንም እውቅና፣ መረዳት እና አንስተን እንድናያቸውም እንፈልጋለን።
ፍትሃዊ እኩልነትን እንደ ቁልፍ እሴት አድርገን እንገነዘባለን እናም የማመላለሻ ስርዓቱ ነጭ ያልሆኑ ማህበረሰቦችን እና የሁሉንም ባለገቢዎች (የተለያዩ ገቢ ያላቸውን)፣ ችሎታዎች እና ዕድሜዎች ፍላጎቶች ማሟላት አለባቸው ብለን እናምናለን። ግባችን የዘር አኩልነት የሰፈነበት እና ማህበራዊ ፍትህ የነገሰበት የማመላለሻ ሥርዓት ለመገንባት ከማህበረሰቦች ጋር አጋርነት መመስረት ነው።
እቅዱ ምን እንደሆነ የበለጠ ለማወቅ፣ የፕሮጀክት ግብዓቶችን እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ለማግኘት እና በእቅድ ሂደቱ ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ድህረ ገጽን ይጎብኙ።
ይሳተፉ
ሲያትል ውስጥ መጓጓዣን እንደገና ለመቅረጽ የእርስዎን እገዛ እንፈልጋለን!
እስካሁን ከእርስዎ የተማርነው ምን አለ?
እያንዳንዳቸውን በመጀመሪያው የተሳትፎው ዙር ወቅት ግብአት እና ሃሳቦችን ያካፈሉትን ሁሉ እናመሰግናለን!
- የዳሰሳ ጥናት ምላሾች: 2,295
- በበይነተገናኝ ካርታችን ላይ የተቀመጡ የወረቀት መርፌዎች ፡ 6,317 — እርስዎ እና ጎረቤቶችዎ ያጋሯቸውን ይገምግሙ!
- አጠቃላይ አስተያየቶች: 336
- የማህበረሰብ ክስተቶች: 44
- ስብሰባዎች: 26
ሁለተኛውን ዙር የማህበረሰብ ተሳትፎ ጀምረናል!
ስለ ማመላለሻ ፍላጎቶችዎ እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች የጠየቅንበትን ክፍለ ጊዜ፣ የመጀመሪያውን ዙር የማህበረሰብ የተሳትፎ ስምሪትን ወቅት አጠናቀናል። ይህም ለወደፊቱ የሲያትል የማመላለሻ ሥርዓት የነበረንን የጋራ ራዕያችንን እንድናዳብር ረድቶናል።
በዙር 2 ወቅት፣ በዙር 1 ላይ ከእርስዎ የሰማነውን እናካፍላለን እና የእርስዎ ግብአት የእቅዱን ራዕይ፣ ግቦች እና አላማዎች እንዴት እንደሚመራ እናሳያለን። እባኮትን ወደፊት እንዴት መዘዋወር እንደሚፈልጉ እና ምን እርምጃዎች እንድንወስድ እንደሚፈልጉ ያካፍሉ።
ማወቅ እንፈልጋለን:
- አዲስ: እስኪ የመጓጓዣ ካርታችንን አንድ ላይ እንፍጠር። በትክክለኛው ፈለግ ላይ ነን?
- የሲያትል የማመላለሻ እቅድ እይታ፣ ግቦች እና አላማዎች ለእርስዎ ትክክል እንደሆኑ ይሰማዎታል?
- በሲያትል ውስጥ ምን ዓይነት የመጓጓዣ ወደፊት ማየት ይፈልጋሉ?
- ግቦቻችንን ለማሳካት ምን ድርጊቶችን መውሰድ አለብን?
ዙር 2 እስከ የካቲት 21 ቀን 2023 ድረስ ይቆያል። የመጨረሻውን የተሳትፎ ዙር ፣ ዙር 3ን በሚያዝያ 2023 ውስጥ እንጀምራለን። የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ረቂቅን መገምገም የሚችሉት በዚህ ጊዜ ነው።
በየሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) አፈጣጠሩ ውስጥ በመሳተፍ፣ ለሁሉም ሰው በተሻለ ሁኔታ የሚሰራ የመጓጓዣ ስርዓት እንድንገነባ ይረዱናል!
የግላዊነት ማስታወቂያ
የእርስዎ ግላዊነት ለእኛ አስፈላጊ ነው። በዚህ ገጽ ላይ የተጋሩት አስተያየቶች ማን እንዳደረጋቸው የማይታወቁ/ ስም-አልባ ናቸው።
በዚህ ገጽ ላይ የገባው የግል መረጃ በዋሽንግተን የህዝብ ምዝገባዎች ህግ ተገዢ ነው እና ለሶስተኛ ወገን ጠያቂ ይፋ ሊደረግ ይችላል። በሲያትል ከተማ፣ የእርስዎን ግላዊነት ለመጠበቅ ቁርጠኞች ነን እናም ማንኛውም ይፋዊ የሚደረጉ መግለጫዎች በህግ መሰረት መደረጉን እናረጋግጣለን። ይህ መረጃ እንዴት እንደሚተዳደር የበለጠ ለማወቅ እባክዎ የእኛን የግላዊነት መግለጫ ይመልከቱ።
በመጀመሪያው የመጓጓዣ ካርታዎች ላይ አስተያየት ይስጡ
እስኪ የመጓጓዣ ካርታችንን አንድ ላይ እንፍጠር። በትክክለኛው ፈለግ ላይ ነን?
መንገዶቻችንን እና የህዝብ ቦታዎችን የምንጠቀምባቸው ብዙ መንገዶች አሉ! STP ን ማዳበር ከመጀመራችን በፊት፣ አራት የመጓጓዣ አውታረ መረብ ካርታዎች (የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የሕዝብ መጓጓዣ፣ እና የጭነት) ነበሩን። ለ STP፣ እነዚያን ካርታዎች እያዘመንን እና ለዛሬ ተግዳሮቶች ምላሽ የሚሰጡ አዲስ ካርታዎችን እየሰራን ነው።
ዛሬ፣ በአንድ ትልቅ የሲያትል ካርታ ላይ ስለሚታየው፣ የእነዚህ አውታረ መርቦች የመጀመሪያ ረቂቆች አስተያየትዎን እንዲሰጡን እንጠይቃለን።
- እግረኛ: በእግር ለሚሄዱ እና ለሚያንከባልሉ ሰዎች
- አዲስ! የሰዎች መንገዶች እና የህዝብ ቦታዎች: ሰዎች በእግር የሚሄዱበት፣ የሚያንከባልሉበት፣ የሚሰበሰቡበት፣ የሚጫወቱበት እና የሚገናኙባቸው ቦታዎች
- ብስክሌት: ብስክሌት ወይም ኢ-ተንቀሳቃሽነት ለሚጠቀሙ ሰዎች (እንደ ባለ ቀላል ሞተር የኤሌክትሪክ ብስክሌት ያለ)
- ትራንዚት/ የህዝብ ማመላለሻ: አውቶብሶችን፣ ቀላል ባቡርን እና ሌሎች የህዝብ ማመላለሻዎችን ለሚወስዱ ሰዎች
- ጭነት: እቃዎችን ለማድረስ
እባክዎ ከታች ያለውን በይነ-ተገናኝ የካርታ ስራ መሳሪያ በመጠቀም የመጀመሪያውን ረቂቅ ካርታዎች ያስሱ።
አስፈላጊ: እነዚህ የመጀመሪያ ረቂቅ ካርታዎች መነሻ ነጥብ ናቸው። እነሱ አዳዲስ በገነባናቸው መገልገያዎች ላይ የተመሠረቱ ማሻሻያዎችን ያካትታሉ፣ የአዲስ ግንኙነቶችን ሀሳብ ይጠቁሙ እና እርስዎ እና ጎረቤቶችዎ በመጀመሪያው የተሳትፎ ምዕራፍ ላይ ለሰጣችሁት ብዙ አስተያየቶች ምላሽ ይሰጣሉ። በእነዚህ ካርታዎች ላይ አሁንም ለውጦችን እያደረግን ነው። ዛሬ እርስዎ በሚሰጡት ግብረ መልስ ላይ ተመስርተን፣ ተጨማሪ ለውጦችን እናደርጋለን።
መሣሪያውን በሙሉ ስክሪን ውስጥ ለማየት እዚህ ጠቅ ያድርጉ።
በረቂቅ ካርታዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ሁለት መንገዶች አሉ:
- ከበይነ-ተገናኝ ካርታው በታች ካለው የአስተያየት ሳጥኑ በኩል አጠቃላይ አስተያየት ይስጡ።
- ከታች ባለው በይነ-ተገናኝ ካርታ ውስጥ፣ በግራ በኩል ባሉት ሌሎች ትሮች ውስጥ ያሉትን የካርታ ንብርብሮች ያስሱ እና ግብረመልስ ለመስጠት ጥቂት የካርታ የወረቀት መርፌዎችን ጣል ጣል አድርጉባቸው።
ምን እንደሚያስቡ ይንገሩን
- በካርታው ላይ ስለሚታዩ አውታረ መረቦች አጠቃላይ አስተያየት አለዎት? ከታች ያለውን የአስተያየት ሳጥን ይጠቀሙ እና አስተያየትዎ ከየትኛው ርዕስ(ሶች) ጋር እንደሚዛመድ ይፈትሹ።
- በአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ አስተያየት አለዎት? በካርታው ላይ የወረቀት መርፌ ለመጣል ከላይ ያለውን በይነ-ተገናኝ የካርታ ስራ ማሳሪያ ይጠቀሙ።
ማስታወሻ
የሲያትል የማመላለሻ እቅድን እንደገና ስንለቅ ፀደይ 2023 ውስጥ እንደገና አስተያየት መስጠት ይችላሉ።
ጸደይ 2023 ውስጥ፣ በእነዚህ አዳዲስ ርዕሶች ላይ የእርስዎን ገብረ መልስ እንጠይቃለን:
- አዲስ! ኩርባ አስተዳደር: ከኩርባው ጋር ተያይዞ ያለ ቦታውን ማን፣ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል
- አዲስ! የተሽከርካሪ ጉዞ: ለአምቡላንሶች፣ ለእሳት አደጋ መኪናዎች፣ እና ሌሎች በተሽከርካሪ መደረግ ያለባቸው ጉዞዎች
- አዲስ! አዲስ እና ብቅ ባይ ተንቀሳቃሽነት: የሚጋሯቸው የቀላል ሞተር ብስክሌቶች፣ ብስክሌቶች፣ ራሳቸውን የቻሉ ተሽከርካሪዎች፣ የሚጋሯቸው/ አብረው የሚሳፈሩ መኪና እና ሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለሚጠቀሙ ሰዎች
ራዕያችንን፣ ግቦቻችንን እና ዓላማዎቻችንን ይገምግሙ
በዙር 1 ውስጥ፣ የእርስዎን የመጓጓዣ የወደፊቱ ያለዎትን እይታ ነግረውናል እና እኛም አዳመጥን! STP አሁን እና ለወደፊትም ለእያንዳንዱ ሰው ሁሉ በተሻለ ሁኔታ የሚሰራ አንድ የማመላለሻ ስርዓት እንዴት እንደምንገነባ በጋራ ራዕያችን፣ ግቦቻችን እና አላማዎቻችን ይመራል።
ስራችንን ይገምግሙ እና ራዕያችንን፣ ግቦቻችንን እና ዓላማዎቻችንን እንድናጣራ ይርዱን!
ራዕይ — በ20 ዓመታት ውስጥ በሲያትል ውስጥ መጓጓዣ ምን እንዲመስል የምንፈልገው
እነዚህ መግለጫዎች በሲያትል ውስጥ የኛን የወደፊት የመጓጓዣ ራዕያችንን ለማንፀባረቅ ያልማል።
ግቦች — ራዕያችንን ለማሳካት ምን ማድረግ እንዳለብን
እነዚህ ስድስት ግቦች ስለወደፊት መጓጓዣችንን በተመለከተ ውሳኔዎችን እንድናደርግ ይረዱናል። የእርስዎ ግብአት የመጨረሻዎቹን ግቦች ቅርጽ ይሰጣቸዋል።
ደህንነት

ደህንነቱ የተጠበቀ የመጓጓዣ የአየር አካባቢዎችን መፍጠር እና ከባድ ጉዳቶችን እና ገዳይ አደጋዎችን ማስወገድ።
እኩልነት

ከመጓጓዣ ጋር የተዛመዱ ልዩነቶችን እና ተያያዥ የሆኑ ጎጂ የማህበረሰብ እና የጤና ተጽእኖዎችን ማስወገድ።
የአየር ንብረት እርምጃ (Climate Action)

የአየር ንብረት ድንገተኛ አደጋ የአሁኑን ወቅታዊ እና ሊመጣ ያለውን የጤና፣ የአየር አካባቢ እና ኢኮኖሚያዊ መዘዞችን ለመከላከል ከትራንስፖርት ጋር የተዛመዱ የአረንጓዴው አየር ልቀትን በከፍተኛ የግፊት ሁኔታ መቀነስ።
መጋቢነት/ ተንከባካቢነት

በከተማዋ በታሪክ ከተገቢው በታች መዋዕለ ንዋይ ሲደረግባቸው የነበሩ ማህበረሰቦችን በማስቀደም አንድ አስተማማኝ የማመላለሻ ስርዓትን ለማሻሻል እና እንዳለ ተንከባክቦ ይዞ ለማስቀጠል የህዝብ ሃብት ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ መመደብ።
ተንቀሳቃሽነት

ሰዎች እና ሸቀጦች/ እቃዎች እንዲደርሱ ወደተፈልጉባቸው ቦታ መድረስ የሚያስችል አስተማማኝ እና በዋጋ ተመጣጣኝነት ያለው የጉዞ አማራጮችን ማቅረብ።
መኖር የሚያስችል

የሚስቡ/ የሚጋብዙ መንገዶችን እና የሰዎች ቦታዎችን መፍጠር።
እነዚህ ግቦች ለእርስዎ ትክክል እንደሆኑ ይሰማዎታል?
ዓላማዎች — ግቦቻችንን እንዴት እንደምናሳካ
የ STP ሂደት በሚቀጥልበት ጊዜ የእርስዎ ግብአት እነዚህን አላማዎች ወደ ስልቶች እና ድርጊቶች እንድንለውጥ ይረዳናል።
ደህንነትን ለማሻሻል መንገዶቻችንን እና የእግረኛ መንገዶቻችንን መንደፍ፣ መስራት፣ እና አስቀድሞ በንቃት መንከባከብ።
በመንገዶቻችን ውስጥ አንድ የባለቤትነት ስሜትን የሚያጎለብት እና የባህል እና የማህበረሰብን ማንነት የሚያስከብሩ መልካም አቀባበል/ የሚጋብዝ እና ተደራሽነት ያለው የህዝብ ቦታዎችን መፍጠር።
ዜሮ-የተበከለ የአየር ልቀት፣ ጤናማ፣ በዋጋ ተመጣጣኝ፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ ለአጠቃቀም የቀለለ እና ተደራሽነት ያለው፣ ብዝሃን የጉዞ አማራጮችን በማበረታታት እና በማቅረብ የሲያትል የተንቀሳቃሽነት እና የአየር ንብረት የድንገተኛ አደጋ ፍላጎቶችን ማሟላት።
ሁሉን የተሸከርካሪ ጉዞዎችን እና የተሄደባቸው የተሸከርካሪ ማይሎች (VMT)ን በመቀነስ እና የአንድን ተሽከርካሪ የሚያስፈልገውን ጉዞዎች በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ በማድረግ የአረንጓዴውን የአየር ብክለት ልቀት መቀነስን ማፋጠን።
ተሳፋሪዎች በአስተማማኝነት ወደሚፈልጉበት ቦታ ቦታዎች በማጓጓዝ፣ ለአብዛኛዎቹ ጉዞዎች የሕዝብ ማመላለሻን ማራኪ የጉዞ ምርጫ ማድረግ።
በመንገዶቻችን እና በመንገዶቻችን የጠርዝ ዝርጊያ/ ኩርባዎች አቀያየሳቸው እና አስተዳደር በኩል የሸቀጦችን እና የአገልግሎቶችን ቀልጣፋ፣ እና ዘላቂነት ያለው እንቅስቃሴ መደገፍ።
በማመላለሻ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች፣ አቀያየሶች እና መዋዕለ ንዋዮች ምክንያት የተከሰቱ ያለፉ ጉዳቶችን እውቅና ለመስጠት እና ከዚያም ያለፈ መፈናቀል እንዳይሆን አውጣጥቶ ለመፍታት፣ በታሪክ ከተገቢው በታች መዋዕለ ንዋይ ሲደረግባቸው የነበሩ ማህበረሰቦችን እና ተፈናቀለው በነበሩ ማህበረሰቦች ውስጥ መዋዕለ ንዋዮችን እና የማህበረሰቦቹን ተሳትፎ ማሳደግ።
የከተማው የማመላለሻ ውሳኔዎች እና መዋዕለ ንዋዮች አጠቃላይ የከተማውን የእድገት ስልት መደገፋቸውን ማረጋገጥ።
ለመጠገን በአዳዲስ አቀራረቦች፣ የፕሮጀክቶች ቅድሚያ አሰጣጥ፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ እና ግልጽነት በመጠቀም ውስብስብ የማመላለሻ ፈተናዎቻችንን እና ኢፍትሃዊ እኩልነትን መጋፈጥ።
እነዚህ ዓላማዎች ለእርስዎ ትክክል እንደሆኑ ይሰማዎታል?
የወደፊቱን ማየት የሚፈልጉትን ይምረጡ
ራዕያችንን ለማሳካት እና የማመላለሻ ግቦቻችንን ለማሳካት ያነሰ መንዳት አለብን። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፣ ለእያንዳንዱ ሰው ሁሉ ያለ መኪና እንዲዘዋወር አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አማራጮችን የሚሰጥ አንድ የማመላለሻ ሥርዓት መገንባት ያስፈልገናል። ወደፊት በሲያትል ውስጥ እንዴት መዘዋወር እንደምንችል፣ የሚሆን ከሆነ እና በምን ያህል ፍጥነት የመጓጓዣ ግቦቻችንን ማሳካት እንደምንችል ይወስናል።
ለሲያትል እነዚህን ሶስት “የመጓጓዣዎች የወደፊት እድል”ን ከግምት ይጨምሩ።
የወደፊት A
በፈለጉ/ ሂደቱ ወቅት ይቆዩ
- የማመላለሻ ስርዓታችንን ደረጃ በደረጃ እየቀያየርን ነው
- እኛ ወደ ግቦቻችን ግስገሳ እናደርጋለን፣ ነገር ግን ብዙዎቹ ከሚደረስባቸው ውጭ ናቸው
ይህ ማየት የሚፈልጉት የወደፊቱ ጊዜ ነው?
የወደፊት A — ተጨማሪ ዝርዝሮች።
ወደፊት A በሲያትል ዙሪያ እንዴት እንደምንዘዋወር እንደገና መልሰን እንደማናስብ ይገምታል። ይህ ማለት ከፍተኛ መጠን ያለው የመኪና ጉዞ እና ዝግ ያለ የሕዝብ መጓጓዣ መውሰድ፣ በእግር መሄድ፣ ብስክሌት መጋለብ እና የማንከባለል ሽግግር ማለት ነው። እንዲሁም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዝግ ያለ ሽግግርን ግምት ውስጥ ያስገባል። የማመላለሻ ግቦቻችንን ለማሳካት ወደዚያ የምናደርገው ግስጋሴ በዝግታ እርምጃ ይከናወናል እና ብዙዎች ግቦች ሊደረስባቸው አይችሉም።
ደህንነት – የትራፊክ ብዛታችን እና ፍጥነታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሂደት ውስጥ ካልቀነሰ ከትራፊክ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን እና ሞቶችንም መቀነስ ለማሳካት የበለጠ ከባድ ነው።
እኩልነት – የትራፊክ አሉታዊ ተፅእኖዎች ነጭ ባልሆኑ ማህበረሰቦች ላይ ያልተመጣጠነ ተጽዕኖ ማድረጉን ይቀጥላል፣ ይህም የመጓጓዣ ስርዓትን ፍትሃዊ እኩልነት ለማግኘት የበለጠ አስቸጋሪ ያደርገዋል።
የአየር ንብረት – የመጓጓዣ ዘርፉ 60 በመቶ ያህል የሚሆነውን የአረንጓዴውን ይዘት ጋዝ ልቀቶችን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ያለ ወደኤሌክትሪክ የመለወጥ እና የመኪና ጉዞ መቀነስ ሌላ፣ የአየር ንብረት ግቦቻችንን መድረስ የሚቻል አይሆንም።
መጋቢነት – በዚህ አካሄድ ከቀጠልን ከጊዜ ወደ ጊዜ የመንገዶቻችንን ጥገና በጥሩ ሁኔታ መጠበቅ ይበልጥ በጣም ውድ ይሆናል። በመኪኖቻችን እና በከባድ መኪናዎች አጠቃቀም መጠን መንገዶቻችን እና ድልድዮቻችን ይባባሳሉ።
ተንቀሳቃሽነት – ለመኪና ጉዞ ቅድሚያ መስጠት ሰዎችን ከእድሎች ጋር ለማገናኘት የጉዞ አማራጮችን ለመጨመር አስቸጋሪ ያደርገዋል።
መኖር መቻል – አዲስ ህዝባዊ ቦታዎች አቀባበልን የመፍጠር እርምጃው አዝጋሚ ይሆናል።
የወደፊት B
መጠነኛ ፍጥነት
- የመጓጓዣ ስርዓታችን ለውጦችን እናፋጥናለን
- አንዳንድ ግቦቻችን ሊደርሱባቸው ይችላሉ
ይህ ማየት የሚፈልጉት የወደፊቱ ጊዜ ነው?
የወደፊት B — ተጨማሪ ዝርዝሮች።
በወደፊት B ውስጥ፣ በመጓጓዣ ስርዓታችን ለውጦችን ማድረግ እና ግቦቻችንን ማሳካት እንጀምራለን። ያም ማለት ተጨማሪ የመጓጓዣ አማራጮች እና ያነሰ የመኪና ትራፊክ ማለት ነው። የበለጠ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችንም ጨምሮ ይህ ወደ ሕዝብ ማመላለሻ፣ ወደ እግር ጉዞ፣ ወደ ብስክሌት መጋለብ እና ማንከባለል አንድ የተፋጠነ ሽግግር ይመራል። ግቦቻችንን ወደማሳካት የምናደርገው ግስጋሴ ከወደፊቱ A በበለጠ የፈጠነ ነገር ግን ከወደፊቱ C ያዘገመ ሆኖ ይከሰታል። ግስጋሴ ግቦቻችንን ወደማሳካት ይደረጋል፣ ነገር ግን ሁሉም ግቦች ሊደረስባቸው በሚቻል አቅም ውስጥ አይደሉም።
ደህንነት – የትራፊክ መጠኖቻቸው እና ፍጥነቶቻቸው ሲቀንስ ከትራፊክ ጋር የተያያዙ ጉዳቶች እና ሞቶች ይቀንሳሉ።
እኩልነት – የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት ያለው የመጓጓዣ ስርአት ሊደረግ ይችላል። ትራፊክን መቀነስ፣ ደህንነትን ማሻሻል፣ እና የጉዞ አማራጮችን መጨመር እንጀምራለን፣ በተለይ የመጓጓዣ ስርአቱ በፊትም እና በቀጣይነትም ተጽኖ ላደረሰባቸው እና እስካሁን በስርአቱ ከተገቢው በታች ተገለግለው ለተጎዱ ሰዎች።
የአየር ንብረት – የመጓጓዣ ዘርፉ 60 በመቶ ያህል የሚሆነውን የአረንጓዴውን ይዘት ጋዝ ልቀቶችን አስተዋፅኦ በማድረግ ኃላፊነት አለበት። ከቅሪተ አካል ነዳጆች/ ከሰል ወደሌላ ፈረቃ ማድረግ የአየር ንብረት ግባችንን ወደማሳካት ግስጋሴ ያደርጋል።
መጋቢነት – የመንገዶቻችን እና የድልድዮቻችን ተባብሶ መበላሸቱ በእነሱ ላይ ካለው የትራፊክ መጠን ጋር የተቆራኘ ነው። የትራፊክ መጠኖችን መቀነስ የመጓጓዣ ስርዓታችንን ጠቃሚ ህይወት ማራዘም ይጀምራል።
ተንቀሳቃሽነት – በመኪናዎች ላይ መተማመንን መቀነስ ለተጨማሪ የጉዞ አማራጮች ክፍተትን ይሰጣል እና በተሻለ ሁኔታ ሰዎችን ከእድሎች ጋር ያገናኛል።
መኖር መቻል – በሲያትል መዘዋወር የበለጠ የሚደሰቱበት ነው እና ከምንወዳቸው ቦታዎች እና ሰዎች ጋር መገናኘት ቀላል ነው።
የወደፊት C
ፈጣን ግስጋሴ
- እኛ በመጓጓዣ ስርዓታችን ላይ የተቀያያሪነት ለውጦችን እናደርጋለን
- ግቦቻችንን ለማሳካት እጅግ የተሻለ አቀማመጥ ላይ ነን
ይህ ማየት የሚፈልጉት የወደፊቱ ጊዜ ነው?
የወደፊት C – ተጨማሪ ዝርዝሮች።
ወደፊት C ሲያትል ዙሪያ እንዴት መንቀሳቀስ እንደምንችል እንደገና ማሰብን ያስችላል። የሕዝብ መጓጓዣ ለመውሰድ፣ በእግር ለመሄድ፣ ብስክሌት ለመጋለብ እና ለማንከባለል እጅግ ፈጣን የሆነውን ሽግግር ከግምት ያስገባል። እንዲሁም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፈጣን ሽግግርን ይደግፋል። ከወደፊት C ጋር፣ ሁሉም የመጓጓዣ ግቦቻችን ተደራሽ ናቸው እና እነርሱን ለማሳካት ወደእነሱ የምናደርገው ግስጋሴ እጅግ በጣም በፈጠነ እርምጃ ይሆናል።
ደህንነት – ለሲያትል እጅግ በጣም አስተማማኝ የወደፊት ጊዜ የሚቻለው የመኪና ጉዞን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ እና የተሻሻለ የጉዞ አማራጮችን በማድረግ በኩል ነው።
እኩልነት – ባልተመጣጠነ ሁኔታ ሲጎዱ የቆዩትን እና ከተገቢው በታች ሲገለገሉ የቆዩትን ማህበረሰቦችን እንዴት እንደምንደግፍ እንደገና በማሰብ፤ አንድ ፍትኀዊ እኩልነት ያለው የመጓጓዣ ስርአት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል። በመጓጓዣ ሥርዓቱ ውስጥ ከተገቢው በታች እየተገለገሉ ለሚቀጥሉት ሰዎች ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት፣ ትራፊክን እንቀንሳለን፣ ደህንነትን እናሻሽላለን፣ እና የጉዞ አማራጮችን እንጨምራለን።
የአየር ንብረት – የመጓጓዣ ዘርፉ 60 በመቶ ያህል የሚሆነውን የአረንጓዴውን ይዘት ጋዝ ልቀቶችን አስተዋፅኦ በማድረግ ኃላፊነት አለበት። ከቅሪተ አካል ነዳጆች/ ከሰል ወደሌላ ፈረቃ ማድረግ የአየር ንብረት ግባችንን ለማሳካት ይረዳል።
መጋቢነት – ነባር መንገዶቻችንን እና ድልድዮቻችንን ለማሻሻል መዋዕለ ንዋይ እናደርጋለን። የተቀነሰ የመኪና ትራፊክ የማመላለሻ ስርዓታችንን ጠቃሚ ህይወት ያራዝመዋል።
ተንቀሳቃሽነት – በመኪናዎች ላይ ያለንን መተማመን በመቀነስ ሰዎችን ከእድሎች ጋር የሚያገናኙ የጉዞ አማራጮችን ለመጨመር ቅድሚያ እንሰጣለን።
መኖር መቻል – የማመላለሻ ግቦቻችንን ወደማሳካት ግስጋሴአችንን ስናፋጥን የህይወታችን ጥራት በእጅጉ የተሻለ ይሆናል እና ሁሉም ሰዎች ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ።
የወደፊት A — ተጨማሪ ዝርዝሮች።
ወደፊት A በሲያትል ዙሪያ እንዴት እንደምንዘዋወር እንደገና መልሰን እንደማናስብ ይገምታል። ይህ ማለት ከፍተኛ መጠን ያለው የመኪና ጉዞ እና ዝግ ያለ የሕዝብ መጓጓዣ መውሰድ፣ በእግር መሄድ፣ ብስክሌት መጋለብ እና የማንከባለል ሽግግር ማለት ነው። እንዲሁም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዝግ ያለ ሽግግርን ግምት ውስጥ ያስገባል። የማመላለሻ ግቦቻችንን ለማሳካት ወደዚያ የምናደርገው ግስጋሴ በዝግታ እርምጃ ይከናወናል እና ብዙዎች ግቦች ሊደረስባቸው አይችሉም።
ደህንነት – የትራፊክ ብዛታችን እና ፍጥነታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ሂደት ውስጥ ካልቀነሰ ከትራፊክ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን እና ሞቶችንም መቀነስ ለማሳካት የበለጠ ከባድ ነው።
እኩልነት – የትራፊክ አሉታዊ ተፅእኖዎች ነጭ ባልሆኑ ማህበረሰቦች ላይ ያልተመጣጠነ ተጽዕኖ ማድረጉን ይቀጥላል፣ ይህም የመጓጓዣ ስርዓትን ፍትሃዊ እኩልነት ለማግኘት የበለጠ አስቸጋሪ ያደርገዋል።
የአየር ንብረት – የመጓጓዣ ዘርፉ 60 በመቶ ያህል የሚሆነውን የአረንጓዴውን ይዘት ጋዝ ልቀቶችን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ያለ ወደኤሌክትሪክ የመለወጥ እና የመኪና ጉዞ መቀነስ ሌላ፣ የአየር ንብረት ግቦቻችንን መድረስ የሚቻል አይሆንም።
መጋቢነት – በዚህ አካሄድ ከቀጠልን ከጊዜ ወደ ጊዜ የመንገዶቻችንን ጥገና በጥሩ ሁኔታ መጠበቅ ይበልጥ በጣም ውድ ይሆናል። በመኪኖቻችን እና በከባድ መኪናዎች አጠቃቀም መጠን መንገዶቻችን እና ድልድዮቻችን ይባባሳሉ።
ተንቀሳቃሽነት – ለመኪና ጉዞ ቅድሚያ መስጠት ሰዎችን ከእድሎች ጋር ለማገናኘት የጉዞ አማራጮችን ለመጨመር አስቸጋሪ ያደርገዋል።
መኖር መቻል – አዲስ ህዝባዊ ቦታዎች አቀባበልን የመፍጠር እርምጃው አዝጋሚ ይሆናል።
የወደፊት B — ተጨማሪ ዝርዝሮች።
በወደፊት B ውስጥ፣ በመጓጓዣ ስርዓታችን ለውጦችን ማድረግ እና ግቦቻችንን ማሳካት እንጀምራለን። ያም ማለት ተጨማሪ የመጓጓዣ አማራጮች እና ያነሰ የመኪና ትራፊክ ማለት ነው። የበለጠ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችንም ጨምሮ ይህ ወደ ሕዝብ ማመላለሻ፣ ወደ እግር ጉዞ፣ ወደ ብስክሌት መጋለብ እና ማንከባለል አንድ የተፋጠነ ሽግግር ይመራል። ግቦቻችንን ወደማሳካት የምናደርገው ግስጋሴ ከወደፊቱ A በበለጠ የፈጠነ ነገር ግን ከወደፊቱ C ያዘገመ ሆኖ ይከሰታል። ግስጋሴ ግቦቻችንን ወደማሳካት ይደረጋል፣ ነገር ግን ሁሉም ግቦች ሊደረስባቸው በሚቻል አቅም ውስጥ አይደሉም።
ደህንነት – የትራፊክ መጠኖቻቸው እና ፍጥነቶቻቸው ሲቀንስ ከትራፊክ ጋር የተያያዙ ጉዳቶች እና ሞቶች ይቀንሳሉ።
እኩልነት – የበለጠ ፍትሃዊ እኩልነት ያለው የመጓጓዣ ስርአት ሊደረግ ይችላል። ትራፊክን መቀነስ፣ ደህንነትን ማሻሻል፣ እና የጉዞ አማራጮችን መጨመር እንጀምራለን፣ በተለይ የመጓጓዣ ስርአቱ በፊትም እና በቀጣይነትም ተጽኖ ላደረሰባቸው እና እስካሁን በስርአቱ ከተገቢው በታች ተገለግለው ለተጎዱ ሰዎች።
የአየር ንብረት – የመጓጓዣ ዘርፉ 60 በመቶ ያህል የሚሆነውን የአረንጓዴውን ይዘት ጋዝ ልቀቶችን አስተዋፅኦ በማድረግ ኃላፊነት አለበት። ከቅሪተ አካል ነዳጆች/ ከሰል ወደሌላ ፈረቃ ማድረግ የአየር ንብረት ግባችንን ወደማሳካት ግስጋሴ ያደርጋል።
መጋቢነት – የመንገዶቻችን እና የድልድዮቻችን ተባብሶ መበላሸቱ በእነሱ ላይ ካለው የትራፊክ መጠን ጋር የተቆራኘ ነው። የትራፊክ መጠኖችን መቀነስ የመጓጓዣ ስርዓታችንን ጠቃሚ ህይወት ማራዘም ይጀምራል።
ተንቀሳቃሽነት – በመኪናዎች ላይ መተማመንን መቀነስ ለተጨማሪ የጉዞ አማራጮች ክፍተትን ይሰጣል እና በተሻለ ሁኔታ ሰዎችን ከእድሎች ጋር ያገናኛል።
መኖር መቻል – በሲያትል መዘዋወር የበለጠ የሚደሰቱበት ነው እና ከምንወዳቸው ቦታዎች እና ሰዎች ጋር መገናኘት ቀላል ነው።
የወደፊት C – ተጨማሪ ዝርዝሮች።
ወደፊት C ሲያትል ዙሪያ እንዴት መንቀሳቀስ እንደምንችል እንደገና ማሰብን ያስችላል። የሕዝብ መጓጓዣ ለመውሰድ፣ በእግር ለመሄድ፣ ብስክሌት ለመጋለብ እና ለማንከባለል እጅግ ፈጣን የሆነውን ሽግግር ከግምት ያስገባል። እንዲሁም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፈጣን ሽግግርን ይደግፋል። ከወደፊት C ጋር፣ ሁሉም የመጓጓዣ ግቦቻችን ተደራሽ ናቸው እና እነርሱን ለማሳካት ወደእነሱ የምናደርገው ግስጋሴ እጅግ በጣም በፈጠነ እርምጃ ይሆናል።
ደህንነት – ለሲያትል እጅግ በጣም አስተማማኝ የወደፊት ጊዜ የሚቻለው የመኪና ጉዞን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ እና የተሻሻለ የጉዞ አማራጮችን በማድረግ በኩል ነው።
እኩልነት – ባልተመጣጠነ ሁኔታ ሲጎዱ የቆዩትን እና ከተገቢው በታች ሲገለገሉ የቆዩትን ማህበረሰቦችን እንዴት እንደምንደግፍ እንደገና በማሰብ፤ አንድ ፍትኀዊ እኩልነት ያለው የመጓጓዣ ስርአት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል። በመጓጓዣ ሥርዓቱ ውስጥ ከተገቢው በታች እየተገለገሉ ለሚቀጥሉት ሰዎች ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት፣ ትራፊክን እንቀንሳለን፣ ደህንነትን እናሻሽላለን፣ እና የጉዞ አማራጮችን እንጨምራለን።
የአየር ንብረት – የመጓጓዣ ዘርፉ 60 በመቶ ያህል የሚሆነውን የአረንጓዴውን ይዘት ጋዝ ልቀቶችን አስተዋፅኦ በማድረግ ኃላፊነት አለበት። ከቅሪተ አካል ነዳጆች/ ከሰል ወደሌላ ፈረቃ ማድረግ የአየር ንብረት ግባችንን ለማሳካት ይረዳል።
መጋቢነት – ነባር መንገዶቻችንን እና ድልድዮቻችንን ለማሻሻል መዋዕለ ንዋይ እናደርጋለን። የተቀነሰ የመኪና ትራፊክ የማመላለሻ ስርዓታችንን ጠቃሚ ህይወት ያራዝመዋል።
ተንቀሳቃሽነት – በመኪናዎች ላይ ያለንን መተማመን በመቀነስ ሰዎችን ከእድሎች ጋር የሚያገናኙ የጉዞ አማራጮችን ለመጨመር ቅድሚያ እንሰጣለን።
መኖር መቻል – የማመላለሻ ግቦቻችንን ወደማሳካት ግስጋሴአችንን ስናፋጥን የህይወታችን ጥራት በእጅጉ የተሻለ ይሆናል እና ሁሉም ሰዎች ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ።
ምን አይነት ድርጊቶችን እንደሚወዱ ይንገሩን
የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የድርጊት የሥራ ዝርዝር
እስካሁን ከእርስዎ በሰማነው ላይ በመመስረት የማመላለሻ ግቦቻችንን ለማሳካት ልንወስዳቸው የምንችላቸው ተግባራትን አቅም ለይተን አውቀናል። እነዚህን የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የድርጊቶች ዝርዝር ብለን እየጠራን ነው። ለወደፊቱ በከተማው ውስጥ እንዴት መዘዋወር እንደምንፈልግ ማሰብ ስንቀጥል በእነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ በሚሏቸው ድርጊቶች ላይ ግብረ-መልስዎን እንፈልጋለን።
በእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ ይሸብልሉ፣ የትኞቹን እንደሚወዱዋቸው እንዲነግሩን በ“ልብ” ላይ ጠቅ ያድርጉ፣ እነዚህ የማመላለሻ ስርዓታችን አካል እንዲሆኑ እና እንዴት እንደሚፈልጉ — ወይም እንደማይፈልጉ — ለመጋራት ለጥያቄዎቹ ምላሽ ይስጡ።
የወደፊት የማመላለሻ ስርዓታችንን እንዲመራ ማህበረሰቡን ማብቃት
የማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማስፋት፣ የውሳኔ አሰጣጥን ለመጋራት፣ እና ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማጎልበት/ ለማሳደግ የማመላለሻ ፍትሃዊ እኩልነት ማዕቀፉን (TEF) ድርጊቶችን እና ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
በእቅድ ሂደታችን ውስጥ ነጭ ያልሆኑ ማህበረሰቦችን እና ያልተወከሉ ቡድኖችን ድምጽ ማዕከል አድርግ
በእኛ ተሳትፎ እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ በታሪክ ውክልና የሌላቸውን ማህበረሰቦች ራዕይ፣ ግቦች እና ፍላጎቶች ቅድሚያ ይስጡ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
በትራንስፖርት ስርዓታችን ውስጥ ያለውን ኢፍትሃዊነት ማወቅ እና መፍትሄ መስጠት
በተጨናነቁ መንገዶች እና አውራ ጎዳናዎች የተጎዱ ማህበረሰቦችን ማገናኘትን እና የመጓጓዣ ተደራሽነትን ማስፋትን ጨምሮ በሰፈሮች ውስጥ ያለማቋረጥ ኢንቨስት በማይደረግባቸው አካባቢዎች ደህንነትን እና እድሎችን ማግኘትን ያሻሽሉ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ለእግረኞች ተጨማሪ ቦታ ይፍጠሩ
የእግረኛ መንገድ ክፍተቶችን እና ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ያላቸውን ቦታዎች በማስቀደም የሲያትል ጎዳናዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ንቁ እና ለሚራመዱ እና ለሚሽከረከሩ ሰዎች ተደራሽ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
የመንገድ ቦታን እንደገና አካፈፍል
አንዳንድ ነባር የትራፊክ መንገዶቻችንን ለብስክሌት፣ ለህዝብ ማመላለሻ፣ ለእግረኛ መንገድ ካፌዎች፣ ወዘተ ወደ ቦታዎች መድገም፣ እንዲሁም አስፈላጊ የትራፊክ መንቀሳቀስን እንጠብቅ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ለሰዎች ተስማሚ መንገዶችን ጨምር
በከተማ መንደሮች እና በመተላለፊያ ማእከሎች ዙሪያ ያሉ መንገዶች ለሰዎች ቅድሚያ መስጠቱን ያረጋግጡ – ደህንነታቸው፣ ልምዳቸው እና ምቾታቸው።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ደህንነትን ለመጨመር የተሽከርካሪ ፍጥነትን ይቀንሱ
መኪናዎችን ወደ ደህና ፍጥነት ለመቀነስ የመንገድ ዲዛይን፣ የምልክት ጊዜ እና የትራፊክ ማረጋጋት ስልቶችን ይተግብሩ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
በሲያትል ዙሪያ ብስክሌት መንዳት ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ ያድርጉት
የተጠበቁ የብስክሌት መስመሮችን ስርዓት ያስፋፉ እና በብስክሌት አውታር ውስጥ ክፍተቶችን ይሙሉ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ለግጭት ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ የደህንነት ኢንቨስትመንቶችን አተኩር
ደህንነትን ለማሻሻል፣ ፍጥነትን ለመቀነስ እና ማህበረሰቦችን ለመደገፍ ከፍተኛ አደጋ የሚደርስባቸው አካባቢዎችን እና መንገዶችን እንደገና ያስቡ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎትን እና መዳረሻን ያሻሽሉ።
ከመጓጓዣ ማዕከላት እና ከቀላል ባቡር ጋር ያለውን ግንኙነት ማሳደግ እና የመጓጓዣ አገልግሎትን በቀን እና በሌሊት ማስፋፋት።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
Photo of Nørreport Station by Gottlieb Paludan Architects and Cobe.
የመተላለፊያ ማዕከሎችን ወደ አቀባበል የማህበረሰብ ቦታዎች ቀይር
በሲያትል የመተላለፊያ ማዕከላት ላይ ብርሃን፣ መንገድ ፍለጋ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የመድረሻ መንገዶችን፣ የእውነተኛ ጊዜ የመተላለፊያ መረጃን፣ የመንገድ ላይ የቤት እቃዎችን፣ የመሬት አቀማመጥን እና የህዝብ ጥበብን ይጨምሩ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ወጪ ለመጓዝ እንቅፋት አለመሆኑን ያረጋግጡ
ሁሉም ሰው የሚፈልጓቸውን ቦታዎች እንዲደርስ የጉዞ አማራጮችን እና ቀላል የገንዘብ ድጋፍን ዘርጋ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
መንገዶቻችን ለአየር ንብረት ለውጥ ዝግጁ ይሁኑ
ለአየር ንብረት ተስማሚ መፍትሄዎችን ኢንቨስት ያድርጉ፣ ለምሳሌ ሙቀትን መቋቋም የሚችሉ ዛፎች፣ የህዝብ ቦታዎች ላይ የውሃ ባህሪያት እና ቀላል ቀለም ያለው ንጣፍ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ዝቅተኛ-ልቀት ዞኖችን ያስተዋውቁ
ወደተዘጋጁት ኮሪደሮች በሚደረጉ ጉዞዎች በመምራት እና የሚራመዱ፣ ቢስክሌት የሚነዱ እና የሚንከባለሉ ከመኪና-ነጻ ወይም ከመኪና ብርሃን ቦታዎችን በማቋቋም የትራፊክ ተፅእኖን ይቀንሱ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
የጭነት እና የጥቅል አቅርቦትን ያሻሽሉ።
እቃዎችን ለማንቀሳቀስ እና ፓኬጆችን ለማድረስ የሚያስፈልጉትን የጉዞዎች ብዛት ይቀንሱ እና እነዚያን ጉዞዎች የበለጠ ቀልጣፋ እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ያድርጉ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
የማህበረሰቡን ፍላጎቶች ለማሟላት መንገድ ዳር ቦታን አስተዳድር
እንደ የአጭር ጊዜ የመኪና ማቆሚያ፣ ማጓጓዣ እና የመንገደኞች ጭነት ያሉ የአካባቢ ፍላጎቶችን ለማስቀደም በንግድ አካባቢዎች ውስጥ ያለውን የገደብ ቦታን ያስተዳድሩ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
የመኪና ጉዞዎችን ይቀንሱ
ሰዎች በመጓዝ ላይ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም አይነት ጉዞዎች የመኪናቸውን ጉዞ እንዲገድቡ እርዷቸው።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሽግግርን ይደግፉ
የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ያክሉ፣ ደጋፊ ፕሮግራሞችን ያዘጋጁ እና የተሸከርካሪ መርከቦችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ያስተላልፉ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ፍትሃዊ የተንቀሳቃሽነት ዋጋ ማውጣት
ሰዎች ወይም ኩባንያዎች የመንገድ ቦታን በሚያሽከረክሩበት ወይም የሚጠቀሙበትን ወጪዎችን እና ጥቅማ ጥቅሞችን በሚያከፋፍል መልኩ የሚያስከፍል ፍትሃዊ የዋጋ አሰጣጥ ስርዓትን ተግባራዊ ያድርጉ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
ውሳኔዎችን ለመምራት ውሂብን ይጠቀሙ
የበለጠ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ ለማድረግ የደህንነት መለኪያዎችን፣ የመጓጓዣ አዝማሚያዎችን እና ቅጽበታዊ መረጃዎችን ጨምሮ የመጓጓዣ ውሂብን ይሰብስቡ እና ያጋሩ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
መንገዶቻችንን ለታዳጊ ቴክኖሎጂዎች አዘጋጅ
የቀጣይ ትውልድ ተሽከርካሪዎችን እና የመንቀሳቀስ መፍትሄዎችን በአስተማማኝ እና በፍትሃዊነት ለማካተት የመንገድ ዲዛይን እና ቴክኖሎጂን ማሻሻል።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
መንገዶችን እና ድልድዮችን አሻሽል፣ በተለይም ያነሰ አገልግሎት በሚያገኙ ማህበረሰቦች ውስጥ
በታሪክ ያነሰ ኢንቨስት በተደረገባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ ማሻሻያዎች ላይ ቅድሚያ በመስጠት ነባር መንገዶቻችንን እና ድልድዮቻችንን በጥሩ ሁኔታ ያቆዩት።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
የትራንስፖርት ስርዓታችንን በጥገና ማሻሻል
ጥገናው በሚከሰትበት ጊዜ ደህንነትን እና ዘርፈ ብዙ የጉዞ አማራጮችን ለማሻሻል እየጨመረ የሚሄድ እርምጃዎችን ያድርጉ።
ይህን ድርጊት ለመውደድ ጠቅ ያድርጉ
አጠቃላይ አስተያየት ይተዉ
በሲያትል የትራንስፖርት እቅድ ላይ አጠቃላይ አስተያየት መስጠት ከፈለጉ፣ እባክዎን ይህንን የአስተያየት ሳጥን ይጠቀሙ።
በሚመጣው ኩነት ላይ ይገኙ
መጪ የርቀት እና በአካል የተሳትፎ እድሎች
ባሉበት እርስዎን መገናኘት!
በሲያትል አካባቢ ባሉ ኩነቶች ላይ ያግኙን።
ስለ STP ምንነት መረጃ ለመለዋወጥ፣ ስለ ሂደቱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እና የመሳተፍ እድሎችን ለመስጠት በኩነቶች ላይ እንገኛለን። በእርስዎ ማህበረሰብ ውስጥ ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት በጉጉት እንጠባበቃለን!
ወደ አርስዎ እንመጣለን!
ወደ ኩነቶችዎ እና ስብሰባዎችዎ እኛን ለመጋበዝ ይህንን ቅጽ ይጠቀሙ።
የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) እየተካሄደ ባለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተደራሽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የተሳትፎ እድሎችን ለማስተናገድ ቁርጠኛ ነው። በአካል ለሚካሄዱ ኩነቶች የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል መመሪያዎችን እየተከታተልን እና በተቻለ ጊዜ ሁሉ ለተሳትፎ እድሎች የርቀት (በአካል ሳይገናኙ) አማራጮችን እናቀርባለን።
ኢሜይል ይላኩልን ወይም በድምጽ መልእክት መስመራችንን ይደውሉ
ስለ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ጥያቄዎች፣ ስጋቶች ወይም አስተያየቶች አሉዎት? ኢሜይል ይላኩልን ወይም በድምጽ መልእክት ይተው እና እንደገና መልሰን እናገኝዎታለን።
የብዙ-ቋንቋ የስልክ መስመራችን ላይ ይደውሉ እና አስተያየትዎን ለማጋራት ወይም ጥያቄ ለመጠየቅ መልእክት ይተው። በመረጡት ቋንቋ መልእክት ይተዉ እና የኛ የስምሪት ቡድን ወይም አንድ አስተርጓሚ መልሶ ደውሎ ለጥያቄዎችዎ መልስ ይሰጥዎታል።
የእኛን የድምጽ መልዕክት መስመር ይደውሉ : 206-257-2114
ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የአካባቢ የአየር ንብረት ግምገማ ሂደት ምንድ ነው?
የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) በግዛት የአካባቢ የአየር ንብረት የአቋም መመሪያ ሕግ (SEPA) ግምገማ ሂደት ውስጥ ያልፋል። SEPA ዕቅድ በማውጣት እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች የአካባቢ ንብረት እሴቶችን በሚገባ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ያረጋግጣል። በ SEPA ሥር፣ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ለከተማው፣ ለህዝብ እና ለሌሎች ኤጀንሲዎች የሲያትል ትራንስፖርት እቅድ የሚጠበቁ የአካባቢ ውጤቶችን የሚያቀርብ አስፈላጊ ጥናት ነው። የበለጠ ለማወቅ የእኛን SEPA እውነታ ወረቀት መገምገም ይችላሉ!
EIS የሲያትል የትራንስፖርት እቅድን እንዴት ይደግፋል?
የተፈጥሮ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ግኝቶች ለግልጽነት ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራሉ እና በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ የማድረግ አስተዋፅዖ ያበረክታል። በተፈጥሮ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ላይ እርስዎ የሰጡት አስተያየቶች በትልቁ የማህበረሰብ ተሳትፎ በኩል ለSTP በአንድ ላይ ተዳምሮ ከተጋራው ግብአት ጋር እየተካተተ ነው። አስቀድመው ያቀረቡትን ማንኛውንም አስተያየት እንደገና ማጋራት አያስፈልግዎትም!
የአስተያየት ጊዜ – ሰኔ 16 – ሀምሌ 29 2022 ፡ በአስተያየቱ ጊዜ አስተያየቶችን ለሰጡን ሁሉ እናመሰግናለን። የእርስዎ ግብአት በተፈጥሮ የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ (EIS) ውስጥ ምን እንደሚካተት እያሳወቀ ነው።
የአካባቢ ተጽዕኖ መግለጫ ረቂቅ (EIS) የሚለቀቅበት እና የ30-ቀን አስተያየት ጊዜ — በ2023 መጀመሪያ: ረቂቁ EIS ከተለቀቀ በኋላ ማህበረሰቡ አስተያየቶችን እንዲያካፍል ተጋብዟል። እነዚህ አስተያየቶች፣ ከምላሾች ጋር በመጨረሻው EIS ውስጥ ተካተዋል።
የመጨረሻ EIS ታትሟል – በ2023 አጋማሽ ላይ ፡ የመጨረሻው EIS፣ በረቂቁ EIS ላይ ለተጋሩ አስተያየቶች ምላሾችን ያካተተ፣ የውሳኔ አሰጣጡን ሂደት ለማሳወቅ ይጠቅማል።
If you need this information translated, please call (206) 257‑2114.
STP 將通過州環境政策法案(State Environmental Policy Act,SEPA) 審查程序。SEPA 確保在規劃和決策過程中全面考慮環境價值. 如果您需要此信息的翻譯版,請致電 (206) 257‑2114。
El Plan de Transporte de Seattle (STP) será sometido al proceso de revisión de la Ley Estatal de Política Ambiental (SEPA). La Ley Estatal de Política Ambiental (SEPA) garantiza que los valores medioambientales se tengan en cuenta de forma exhaustiva durante los procesos de planificación y toma de decisiones. Si necesita esta información traducida, llame al (206) 257‑2114.
STP sẽ trải qua quá trình xem xét về Đạo Luật Chính Sách Môi Trường của Tiểu Bang (State Environmental Policy Act, SEPA). SEPA đảm bảo các giá trị môi trường được xem xét kỹ lưỡng trong quá trình lập kế hoạch và đưa ra quyết định. Nếu quý vị cần có bản dịch thông tin này, vui lòng gọi số (206) 257‑2114.
የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) በስቴት የአካባቢ የአየር ንብረት የአቋም መመሪያ ሕግ (SEPA) ግምገማ ሂደት ውስጥ ያልፋል። SEPA ዕቅድ በማውጣት እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች የአካባቢ ንብረት እሴቶችን በሚገባ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ መረጃ እንዲተረጎምልዎ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ(206) 257‑2114 ይደውሉ።
STP waxay mari doontaa nidaamka dib u eegista sharciga siyaasada deegaanka ee Gobolka (SEPA). SEPA waxay hubisaa in qiyamka deegaanka si fiican loo tixgeliyo inta lagu jiro qorshaynta iyo geedi socodka go'aan qaadashada. Hadii aad u baahan tahay macluumaadkan oo turjuban, fadlan la hadal (206) 257‑2114.
STP는 주 환경 정책법(State Environmental Policy Act, SEPA)의 검토 과정을 거칠 것입니다. SEPA는 계획 및 의사 결정 과정에서 환경 가치가 철저히 고려되도록 합니다. 이 정보의 번역본이 필요한 경우, (206) 257‑2114 으로 전화하십시오.
Ang STP dadaan sa proseso ng pagsusuri ng State Environmental Policy Act (SEPA). Tinitiyak ng SEPA na ang mga kinahahalagahan sa kapaligiran ay lubusang maisasaalang-alang habang nagpaplano at sa proseso ng paggawa ng desisyon. Kung kailangan mo ang impormasyon na ito na nakasalin sa (206) 257-2114.
ስለእርስዎ የበለጠ ይንገሩን
ቀጣይ እርምጃዎች
ወደየት እያመራን ነው
የዕቅድ ሂደቱ በጥር 2022 ተጀምሯል፣ እና በ2023 ጸደይ የህዝብ ግምገማ እቅድ ይኖረናል ብለን እንጠብቃለን። በሂደቱ እስከ መጨረሻ ፣ ልምዶችዎን ለማካፈል እና እቅዱን ለመገምገም፣ አስተያየት ለመስጠት እና ለማገዝ እድሎች ይኖሩዎታል። በሂደቱ ላይ እንደተዘመኑ ለመቆየት እዚህ ተመልሰው ያረጋግጡ።
የጊዜ መስመር
ግንቦት –
ነሐሴ 2022
ዙር 1 የሕዝብ ተሳታፊነት በዚህ ዙር ወቅት፣ ለ STP የጋራ ራዕይ ለመመስረት ከህብረተሰቡ ጋር ሰርተናል። በሲያትል አካባቢ ስትዘዋወሩ ቅድሚያ ስለሚሰጧቸው ነገሮች፣ ተግዳሮቶችዎ እና ፍላጎቶችዎ ጠይቀናል።
መስከረም 2022-ማርች 2023
የህዝብ ተሳትፎ ዙር 2 (እኛ እዚህ ነን) በዚህ ደረጃ፣ በምዕራፍ 1 ላይ ከእርስዎ የሰማነውን እናካፍላለን እና የእርስዎ ግብአት የእቅዱን ራዕይ፣ ግቦች እና አላማዎች እንዴት እንደሚመራ እናሳያለን። እባኮትን ወደፊት እንዴት መዘዋወር እንደሚፈልጉ እና ምን እርምጃዎች እንድንወስድ እንደሚፈልጉ ያካፍሉ።
ሚያዚያ –
ሰኔ 2023
ዙር 3 የሕዝብ ተሳታፊነት የSTP ረቂቁን ለማህበረሰቡ አካፍለናል እና በትክክለኛው ፈለግ ላይ መሆናችንን ለማረጋገጥ የእርስዎን ግምገማ እና ግብረ-መልስ እንጠይቃለን።
በጋ 2023
የሲያትል የማመላለሻ እቅዱን ይጨርሱ!
ስለ STP ዝመናዎች እና መጪ ዕድሎች ለመሳተፍ፣ ለኢሜይል ዝመናዎች መመዝገብዎን ያረጋግጡ።
ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ?
እቅዱ ምን እንደሆነ የበለጠ ለማወቅ፣ የፕሮጀክት ግብዓቶችን እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ለማግኘት እና በእቅድ ሂደቱ ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የሲያትል የማመላለሻ እቅድ ድህረ ገጽን ይጎብኙ።
የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ለማዘጋጀት ስለተሳተፉ እናመሰግናለን! የጋራ ፍላጎታችንን የሚያሟላ የመጓጓዣ ስርዓት ለመፍጠር ከእርስዎ እና ከጎረቤቶችዎ ጋር መስራታችንን ለመቀጠል እንጠባበቃለን።
እንደተገናኙ ይቆዩ
ለሲያትል የማመላለሻ እቅድ የኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ:
ጥያቄዎች፣ ስጋቶች ወይም አስተያየቶች አሉዎት?
ኢሜይል ይላኩልን: STP@Seattle.gov
የእኛን የድምጽ መልዕክት መስመር ይደውሉ: 206-257-2114